EN
Kebreab Demeke (b. 1987, Ethiopia) received an MFA in Art and Public Space from the Oslo National Academy of the Arts in 2017 and a BFA with a specialization in painting from ASFAD, Addis Ababa University in 2010.
Kebreab’s art practice often explores shifts in cultural life and political identity in Ethiopia as well as the influence of international experiences over the years. His works seek to unveil and transcribe existing and forgotten knowledge that has changed across generations. The visuals in his works reflect complex historical realities of twentieth and twenty-first century Ethiopia, in relation to contemporary political and cultural contestation in the country and around the globe.
Kebreab creates his artworks across a range of media, including mixed media painting, printmaking, performance, and installation.
AMH
ክብረአብ ፡ ደመቀ ፡ ሚያዚያ ፲፱፯፱ ፡ በአዲስ አበባ፡ ከተማ፡ ተወለደ። የመጀመሪያ፡ እና፡ ሁለተኛ፡ ደረጃ፡ ትምህርቱን፡ በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ትምህርት ቤት ተከታትሏል። በመቀጠል፡ ለስዕል፡ ባለው፡ ፍላጎት፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፡ አለ የስነጥበብ እና ዲዛይን ት/ቤት፡ በቀለም ቅብ፡ ትምህርት ክፍል በመጀመሪያ ዲግሪ አጠናቋል። ከ ፪፻፫-፪፻፯ ባሉት፡ አራት፡ አመታት፡ በስቱዲዮ፡ ስራ እና፡ በተለያዩ፡ የስነጥበብ፡ አውዶች፡ ላይ፡ በመሳተፍ፡ ልምዱን፡ አዳብሯል።
በመቀጠል፡ የሁለተኛ፡ ዲግሪ፡ ጥናቱን፡ በኖርዌይ፡ ሀገር፡ ኦስሎ፡ ከተማ፡ ስነ ጥበብ፡ እና ህዝባዊ ቦታዎች፡ ላይ፡ ትኩረቱን፡ በማድረግ፡ ትምህርቱን፡ አጠናቋል። ከ፪፲፻፲፰ ፡ ጀምሮ፡ በዛው፡ ኦስሎ፡ ከተማ፡ የስቱዲዮ፡ ስራውን፡ እና፡ ጥናቶችን፡ እያደረገ፡ ይገኛል።
የክብረአብ፡ ደመቀ፡ የስነጥበብ፡ ስራዎች፡ እና፡ ጥናቶች፡ ዋና፡ ትኩረታቸው፡ በ20ኛው፡ እና 21ኛው፡ ክፍለ ዘመን፡ በኢትዮጵያ፡ የተከናወኑ፡ የነበሩና፡ በአሁኑም፡ ሰዓት፡ እየተከናወኑ፡ ያሉ፡ አበይት፡ የፖለቲካ፡ እና፡ ባህል፡ እውነቶችንና፡ ለውጦችን፡ ይዳስሳሉ ::
